Missions

ራዕይ
ሰዎች ፍጹም የሕይወት ለውጥ የሚያመጣውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በእርግጥ አግኝተው በቃሉና በመንፈሱ በመመራት እንዲኖሩ በመርዳት የእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ በመሆን ጌታን ማክበር

ተልእኮአችን
በአካባቢያችን እና ከዚያም ውጭ ያሉትን ሰዎች ለደኅንነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እየጋበዝን በልውጠት ለእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ማስታጠቅ

ዓብይ እሴቶች
የቃሉ ሥልጣናዊነት – ቃላችንና ተግባራችን የሚለካው በእግዚአብሔር ቃል ነው
የክርስቶስ ማእከላዊነት – የምናደርገው ነገር ሁሉ ክርስቶስን የሚያከብር ነው
በጸሎት ተደጋፊነት – በምናደርገውና ልንሆነው በምንመኘው ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ተደጋፊዎች ነን
ምግባረ ሙላት – የእግዚአብሔርን ሐሳብ በመንፈስ ቅዱስ በመመራት በምግባረ ምሉእነት እንፈጽማለን
አንድነት – የክርስትናን ኑሮ በፍቅርና በኅብረት እየኖርን ለአገልግሎት መሰጠታችን በሙሉ ማንነት ነው
የትንንሽ ቡድኖች ተሳትፎ – የጋራ ጥንካሬአችን የተለያዩ ትናንሽ ቡድኖቻችን የጽናት ውጤት ነው
መንፈሳዊ ጤንነት ያለው ቤተ ሰብ – ጤናማ ቤተሰብ የሕብረታችን ኃይል ነው
የአገልግሎት አቀራረብ አቋም – አገልግሎታችን ሰውን በሁለእንተናው ለመድረስና በአገልግሎት በአፈጻጸም የላቀ ሆኖ መገኘት